image
image
image
image
image

በጋራ ሆነን የአረንጓዴ አሻራን በማኖር ስራችን ሀገራችን ዘመን የማይሽረው ታሪክ አስቀምጣለች።

ሰኔ 16, 2018
ባለፉ ሰባት ዓመታት እንደሀገር በሁሉም ኢትዮጵያዊ ትብብር 48 ቢሊዮን ችግኝ በመትከል ታሪካዊ እና አስደማሚ አሻራ አኑረናል። በከተማችንም ባለፋት ሰባት ዓመታት 90 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ ሽፋናችንን እጅግ ዝቅተኛ ከነበረበት 2 .8 በመቶ ወደ 24 በመቶ ማድረስ ችለናል። በአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብራችን የተራቆቱ አካባቢዎች አረንጓዴ ለብሰዋል፤ የነጠፉ ወንዞች እና አካባቢዎች ማንሰራራት ችለዋል። አዲስ አበባችንም ንፁህ፣ ውብ፣ ለመኖር ምቹ እና የቱሪስት ማዕከል መሆን ችላለች። የምንተክለው ተስፋን፣ ልማትን፣ ልምላሜን፣ ጥላን፣ ምግባችንን ብሎም ብልፅግናን ነው። የምንተክለዉ ለዛሬ ጥቅማችን ብቻ ሳይሆን ለትውልድ እዳን ሳይሆን የልምላሜና የብልፅግና ምንዳን ለማውረስ ነው ። ዛሬ በከተማችን 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር በተገኙበት በበሻሌ ወንዝ ዳርቻ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂደናል። ውድ የከተማችን ነዋሪዎች በወንዝ ዳርቻዎች፤ በጤና፣ ትምህርትና በሃይማኖት ተቋማት፤ በግል ሴክተሮች እና በጎዳናዎች ለምግብነት የሚውሉ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን፣ የጥላ እና የውበት ዛፎችን በመትከል ከተማችን ውብ፣ ጽዱ ኢረንጓዴና ለኑሮ ምቹ ከተማ ለማድረግ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ህፃን አዋቂ ሳንል ሁሉም ዜጋ በጋራ በመሆን እንድናሳካው ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። ችግኝ መትከል ብቻ በቂ አይደለም እንክብካቤን ይፈልጋል ። ስለሆነም የተከልናቸውን ችግኞች መከታተል፤ መንከባከብ ይኖርብናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መልዕክትዎን ይላኩ