Welcome to Addis Ketema Subcity Design and Construction Works Office!       እንኳን ወደ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ ከተማን የሚመጥኑ የህዝቡን ፍላጎት ሊያሟሉ የሚችሉ ወጪ ቆጣቢ ዲዛይኖችን በማዘጋጀት የመንግስት ህንጻዎችን ገንብቶ ለነዋሪዎቿ ተደራሽ ለማድረግ ይተጋል!

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

ከተማችን ለረጅም ዓመታት ሲጫናት ከቆየው ድህነትና ኋላ ቀርነት በማላቀቅ ታሪካችንን ለማደስና ለተያያዝነው የለውጥ ጉዞ መንግስት የቀረጻቸውን ልማታዊ አቅጣጫዎች፣ ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች መሠረት እስከ 2022 ባለው የዕድገት ምዕራፍ ውስጥ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ነዋሪዎችን መፍጠር የሚያስችል ራዕይ ተቀርጾ እየተተገበረ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በማሳካት ረገድ ባለፉት ዓመታት በከተማዋ ስር ሰዶ የቆየውን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች በዘላቂነት በመቅረፍ ፈጣንና ፍትሃዊ ልማት ለማረጋገጥና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት ግንባታ ያካሄዳቸው እንቅስቃሴዎች ጅምር ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ ሆራ ተስፋዬ , የአዲስ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

አቶ ወንድወሰን ጽጌ ጀማነህ;
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት አስተባባሪ

የጽ/ቤቱ አስተባባሪ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናዉናል:-
  • በክ/ከተማዋ የሚገነቡ ግንባታዎች በጊዜ፣ በጥራትና በወጪ ቆጣቢነት ከመገንባት ባሻገር ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ደረጃውን የጠበቀ የግንባታ ግብዓት ፍተሻ ማድርግ፤ ተቋማት ከግንባታ ፍላጎት መለየት ጀምሮ በግንባታ ሂደትና በርክክብ ወቅት የሚጠበቅባቸውን በግልጽ በማስቀመጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ከመከሰታቸው በፊት በማረም ስራን ማቀላጠፍ
  • ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርአት ለማስፈን፣
  • አገልግሎት አሰጣጡ በተጠናው ስታንዳድ መሰረት እንዲሰጥ ለማድረግ

የጽ/ቤቱ ቡድን መሪዎች

አቶ

የምህንድስና ግዥ ቡድን መሪ

አቶ ሀይለማርያም ደንግሽ

የኮንትራት አስተዳደር ቡድን መሪ

አቶ ኤልያስ ወርቁ

የፕሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ዝግጅት ቡድን መሪ

አቶ መካሻ ክፍሌ

የመንግስት ኮንስትራክሽን ኦዲት ቡድን መሪ

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡