በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የኮንስትራክሽን ኦዲት ቡድን

በግንባታ ፕሮጀክቶች የክዋኔ ኦዲት (Performance Audit) ስር ያሉ ዝርዝር ተግባራት

  • የመንግስት ግንባታዎች አፈጻጸም የምርመራ ስራዎችን ኦዲት ለማድረግ ከአስገንቢው መ/ቤት ጋር የስራ ትስስር ስርዓት መዘርጋት፣
  • የግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም የስጋት አካባቢ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፣
  • የኦዲት ፕሮግራም ማዘጋጀት፣ በግንባታ ፕሮጀክቶች አሰራር አግባብነትና የአፈጻጸም ውጤታማነት ላይ ምርመራ ማካሔድ፤
  • በየኘሮጀክትና ኮንትራት ስራ አፈፃፀም መመርመሪያ ፎርማት ማዘጋጀት፣በዳሰሳ ጥናት የተለዩ ግንባታዎች አስፈላጊ ሰነዶችን መረካከቢያ ቅጽ በማዘጋጀት ከኦዲት ተደራጊ አካል መረከብ፣
  • የአፈፃፀም ምርመራ (Performance Audit) ከኦዲት ተደራጊ ጋር የመግቢያ ውይይት(Entry Conference) ማድረግ
  • አግባብነት ያላቸው አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና PPA በግንባታው ዲዛይንና ኮንትራት አፈጻጸም በትክክል ተፈፃሚ መሆናቸውን ምርመራ (Performance Audit) ማካሄድ፣
  • በሰነድ ላይ ግልጽነት የሌላቸውን የግንባታው አፈጻጸሞች የመስክ ምርመራ ማካሄድ የታዩ እንከኖችን መለየትና በግኝት ማካተት፣
  • በክዋኔ ኦዲት ግኝቱ ላይ የክፍሉ ቡድን መሪ፣ኦዲት ተደራጊ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት የመውጫ ውይይት ማካሄድ፣ግብዓቶችንና የተደረሰባቸውን ስምምነቶች አካቶ ሪፖርት ማዘጋጀት፣
  • የኦዲት አስተያየት የተሰጠባቸውን ጉዳዮች ላይ ክትትል በማድረግ የእርምት እርምጃዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን መከታተል፣ የማሻሻያ ሐሳብ ማቅረብ፣
በግንባታ ፕሮጀክቶች የመጨረሻ ክፍያ (Final Payment Audit) ኦዲት ስር ያሉ ዝርዝር ተግባራት
  • ግንባታቸው ተጠናቆ ጊዜያዊ ርክክብ/Provisional Acceptance) የተደረገባቸውን የመንግስት ግንባታዎች መለየት
  • የመጨረሻ ክፍያ ኦዲት አስፈላጊ ሰነዶች ከግንባታ ባለቤት እንዲቀርቡ በደብዳቤ መጠየቅና መቀበል፣የመጨረሻ ክፍያ ኦዲት አስፈላጊ ሰነዶች ከግንባታ ባለቤት እንዲቀርቡ በደብዳቤ መጠየቅና አረጋግጦ መረከብ፣
  • የግንባታ ፕሮጀክቶችን የተሰራውን ግንባታ ስራ(excuted works) በውለታ ከተያዘው የስራ መጠን፤ከዲዛይን ወይም ድሮዊንግና specification አንጻር ምርመራ ማድረግ ልዩነቶችን መለየት፣
  • ተጨማሪ የስራ ትዕዛዝ (Variation Orders) እና ሌሎች ከውለታ ሰነድና ዲዛይን(ድሮዊንግ) ላይ የሌሉ የግንባታ ስራዎች(Excuted works) በአግባቡ መጠናቀቃቸውን የመስክ ምርመራ እና ልኬቶችን መውሰድ፣
  • ከtake off, BOQ and Grand Summary ላይ ልዩነት የተፈጠረባቸውንና በመስክ ምልከታ የተገኙ ግኝቶች ላይ ከስራ ተቋራጩ ጋር መተማመን ላይ መድረስና የፕሮጀክቱን የመጨረሻ ክፍያ ኦዲት ሪፖርት ማጠናቀር፣
  • የመጨረሻ ክፍያ ኦዲት ግኝቶች የማስተካከያ እርምጃዎች ተፈጻሚ መደረጋቸውን መከታተል፣

ዓላማ 1. የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ኦዲት ስራዎች ማከናወን

የክዋኔና ፋይናንሻል ኦዲት የተደረገላቸው ፕሮጀክቶች ብዛት

  • ተግባር 1. በበጀት ዓመቱ 2 ጊዜ የስጋት አካባቢ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፣ በጥናቱ ውጤት መሰረት ረቂቅ የኦዲት ፕሮግራም ማዘጃጀት፣
  • ተግባር 2. ለ 12 ፕሮጀክቶች የፕሮጀክት ክዋኔና ፋይናንሻል ኦዲት ማካሄድ፣
  • ተግባር 3. ዘርፉ በሚመራባቸውና አግባብነት ያላቸው አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች በትክክል ተፈፃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በበጀት ዓመቱ 2 ጊዜ የአፈፃፀም ምርመራ ማካሄድ፣
  • ተግባር 4. ተቋሙ በተገቢው ውለታና ስምምነት መሠረት መፈፀሙን ለማረጋገጥ በበጀት ዓመቱ 12 የኘሮጀክትና ኮንትራት ስራ አፈፃፀም ኦዲት ማካሄድ፣
  • ተግባር 5. ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ልዩ ምርመራ የሚፈልጉ 5 የኦዲት ሥራ በበጀት ዓመቱ ማካሄድ፣

በፕሮጀክት ኦዲት የተመረመሩ የመጨረሻ ክፍያዎች ብዛት

  • ተግባር 1. ለ12 ፕሮጀክቶች የፕሮጀክቶችን የመጨረሻ ክፍያ ፋይናንሻል ኦዲት ስራ በማከናወን ለሚመለከተው ክፍል ማሳወቅ ተፈጻሚነቱን መከታተል

በተገኙ የክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ላይ የተወሰደ እርምጃ

  • ተግባር 1. በክዋኔ ኦዲት የተገኙ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ ተገቢ የሆነ አግባብ ያለው ርምጃ መውሰድ

  • ተ.ቁ
  • የክዋኔ ኦዲት እንዲደረግባቸው
    የተመረጡ ፕሮጅከቶች
  • ኮንትራክተር
  • ኦዲት የተደረጉ የመጨረሻ
    ክፍያዎች ዝርዝር
  • ኦዲቱ የተጀመረበት
  • የክዋኔ ኦዲቱ
    የተጠናቀቀበት ቀን
  • የኦዲት ግኝቶች ቫትንጨምሮ
  • 1

  • --

  • --

  • --